ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝም- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሐምሌ 14/2013 (ዋልታ) – ድል ያለ መሥዋዕትነት አይገኝም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጀግናው ሠራዊታችን የሀገራችንን ክብር፣ ነጻነት እና ሉዓላዊነት የሚያስከብረው የላብና የደም ዋጋ ከፍሎ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ይሄንን ተመን የማይገኝለት ዋጋ ሲከፍል ደግሞ ሕዝብ እና መንግሥት ከጎኑ መቆም አለባቸው ብለዋል።

እንደ ወታደር ዓለሚቱ አምባ ያሉ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የተጎዱ የሠራዊት አባላት ለጀግንነታቸው የሚመጥን ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ እየሠራን ነው ሲሉም አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት የሕክምናና የሰው ሠራሽ አካል ድጋፍ ማድረጊያ ማዕከላትን እያጠናከርን ነው ያሉ ሲሆን፣ ማኅበራዊ ሕይወታቸውን ለመደገፍ የሚያስችል ሥራም እየሠራን ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ለእነርሱ የማትሆነው የለም ሲሉም አመልክተዋል።