ዶ/ር ሊያ በ4ኛው የዱባይ ጤና ፎረም ላይ በዘርፉ የኢትዮጵያን ልምድ አካፈሉ

የካቲት 27/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት በማሳደግ ዙሪያ የኢትዮጵያን ልምድ አካፍለዋል፡፡

በዱባይ ጤና ጥበቃ ባለስልጣን በተዘጋጀው 4ኛው የዱባይ ጤና ፎረም ላይ በመሳተፍ “በጤና አጠባበቅ አቅርቦት ላይ ጥራትን እና ብቃትን ማሻሻል” የኢትዮጵያን የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ዋና መሰረት በማድረግ ጥራትን በማሳደግ ዙሪያ ልምድ አካፍለዋል፡፡
ሚኒስትሯ ከዱባይ ጤና ባለስልጣን፣ ናባዳት ኢኒሼቲቭ፣ ኑር ዱባይ ፋውንዴሽን እና ቪፒኤስ ጤና ጥበቃ ጋር በልዩ ልዩ እና የመጀመሪያ ደረጃ ክብካቤ ዙሪያ ባሉ የትብብር ዘርፎች ላይ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይቶች ማካሄዳቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ዶክተር ሊያ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መንግሥት እና የግል ተቋማት በኢትዮጵያ በተለያዩ የጤና ልማት ሥራዎች ላይ ላደረጉት ትብብር እና ድጋፍ ምስጋናቸውንም አቅርበዋል።