ዶ/ር አብርሃም በላይ ለኢድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) – የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ለህዝበ ሙሰሊሙ እንኳን ለ1ሺህ 442ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ይህን በአል ስናከብር አንድነታችን ይበልጥ የምናጠናክርበትና በተለያዩ ቦታዎች የተፈናቀሉ ወገኖች የምናግዝበት በአል ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም የተቸገረን በመርዳትና በመተሳሰብ መሆን አለበት ብለዋል ዶ.ር አብርሃም በላይ በመልእክታቸው፡፡