ጃፓን 30 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ እርዳታ አደረገች

ጥቅምት 16/2014 (ዋልታ) የጃፓን መንግሥት 30 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ እርዳታ አደረገ፡፡

በርክክብ መርሃ ግብሩ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ  የተገኙ ሲሆን በጃፓን እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል በተደረገው ስምምነት መሰረት የቀረበ የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ የመጀመሪያውን ዙር አቅርቦት ያስረከቡ ሲሆን 15 ተንቀሳቃሽ ኤክስሬይ ማሽኖችና ለተለያዩ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት የሚውሉ ሌሎቸ ግብኣቶችን አስረክበዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ  በጤናው ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመስራት ይህ ስምምነት ፈር ቀዳጅ ነው ብለዋል።

በቁምነገር አሕመድ