ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ ነው

ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከትናንት ጀምሮ በግንባር ተገኝተው አመራር እየሰጡ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ነው።

በመግለጫቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት ጀምሮ በግንባር አመራር እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ፋብኮ መረጃ ሌሎች አመራሮችም የኅልውና ዘመቻውን በመቀላቀል ወደ ግንባር መዝመታቸውን ነው የገለጹት፡፡

መደበኛ ሥራዎች እንዳይስተጓጎሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እየተመራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመታቸው በርካቶችን ያነቃቃና በርካቶች እንዲከተሏቸው አድርጓልም ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመት የአመራር ብቃታቸውንና የቆየ የአይበገሬነት ታሪክን ያሳያልም ነው ያሉት።