ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለመሪዎች አሸኛኘት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመት ላይ የታደሙት የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኢል ኡመር ጌሌህ እና የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡኻሪ ዛሬ ወደ አገራቸው አቅንተዋል።

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

በአሸኛኘት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃን ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ ትናንት ምሽት ወደየአገራቸው ሲያቀኑ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።