ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከስሎቪኒያው አቻቸው ጃኔዝ ጃንሳ ጋር ተወያዩ

የካቲት 10/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቪኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኔዝ ጃንሳ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በብራስልስ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን የኢትዮጵያና የስሎቪኒያ ወዳጅነት ስለማጠናከር እንዲሁም ስለቴክኒክ እና ኢኮኖሚ ትብብር ከስሎቪኒያው አቻቸው ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።