ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

ጥር 29/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንውሚ አዴሲና ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይታቸው በኢትዮጵያ የመልማት ሂደትና አማራጮች እንዲሁም ግንኙነታቸውን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ ከአኅጉራዊው ባንክ ፕሬዝዳንት ጋር የጎንዮሽ ውይይቱን ያደረጉት በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡