ጠ/ሚ/ር ዐቢይ  ለኢትዮጵያዊያን ጥሪ አቀረቡ

ጥቅምት 24/2014 (ዋልታ) ወቅቱ አሸባሪው ሕወሓት የሚቀበርበት እንጂ ኢትዮጵያ የምትፈርስበት አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
በአገር መከላከያ ሚኒስቴር ጦር ኃይሎች ግቢ የጥቅምት 24 ሰማዕታት ሲታሰቡ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በእኛ መስዋዕትነት የምትቀጥል አገር ለመሆኗ ቃል ኪዳን የምንገባበት ቀን ነው ብለዋል፡፡
ወቅቱ አሸባሪው ሕወሓት የሚቀበርበት እንጂ ኢትዮጵያ የምትፈርስበት አይደለም በማለትም፤ ኢትዮጵያ በማጎሳቆል ትፈርሳለች ብለው የሚያስቡ ኢትዮጵያ የማትፈርስ ለመሆኗ የዜጎቾ አንድነት ዋስትና ነው ብለዋል፡፡
ጠላቶች ለኢትዮጵያ አስፍተው በቆፈሩት ጉድጓድ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ቆመው ጠላቶቿን ይቀብሩበታል፤ ያዋርዱበታልም ብለዋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እኔም ለአገሬ ወታደር ነኝ በሚል ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም፣ ሰራዊቱን በመቀላቀል እና በመዝመት የኢትዮጵያን ጠላቶች ለማዋረድ ጊዜው አሁን ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!