ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ስለኢትዮጵያዊነት

ጳጉሜ 1/2013 (ዋልታ) ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያዊያን የመተሳሰሪያ ማንነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
‹‹ኢትዮጵያዊነት የኢትዮጵያውያን የመተሣሠሪያ ማንነት ነው። ብዝኃ ባህል፣ ብዝኃ ቋንቋ፣ ብዝሃ እምነት፣ ብዝኃ አመለካከት ያለንን ኢትዮጵያውያን አንድ አድርጎ ለአንድ ሀገራዊዓላማ የሚያቆመን ዕሴት-ኢትዮጵያዊነት ነው።›› ሲሉ በቲውተር ገፃቸው ጽፈዋል፡፡

አክለውም ‹‹ለኢትዮጵያዊነታችን ብዝኃነታችን ማገሩ፣ ጀግንነታችን አጥሩ፣ አንድነታችን ዓምዱ፣ ነጻነታችን መንገዱ ነው ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።›› መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!