ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በተገኙበት የወታደሮች ምርቃት

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) የሁርሶ ኮንቲንጅንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ3ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ምልምል ወታደሮች አያስመረቀ ነው።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፕሮግራሙ ለኢትዮጵያ መስዋአት ለሆኑ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል።

ተመራቂዎቹ ለሙሉ ወታደርነት የሚያበቃውን መሰረታዊ የመከላከያ ስልጠና የወሰዱ ናቸው። ወታደራዊ ትርኢት ለታዳሚው ያቀረቡት ምልምል ተመራቂዎች በሀገር የተጣለባቸውን አደራ በብቃት ለመወጣት ቃለ መሀላ ይፈፅማሉ።

(በደምሰው በነበሩ)