ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ነገ ለሕዝብ ተወካዮች ጥያቄ ምላሽ ይሰጣሉ

ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

የካቲት 14/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነገ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት በተነሱላቸው ጥያቄዎች ላይ ምላሽ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታወቀ።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ረገድ ያለውን የመንግሥታቸውን እንቅስቃሴና ተያያዥ ጉዳዮች የተመለከተ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ነው የሚጠበቀው።