ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ኅብረት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ኅዳር 30/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ኅብረት መስራች እንደመሆኗ ሉኣላዊነቷ በፅኑ መከበር እንዳለበት ከመንግሥታቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ጋር በስልክ ሲወያዩ አፅንኦት እንደሰጡ አሳውቀዋል።