ጠ/ሚ ዐቢይ ለሼህ መሐመድ ቢን ዛይድ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 6/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአዲሱ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የአንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት “በሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በሳል አመራር በሀገሪቱ ዕድገት እና ብልጽግና እንዲመጣ ልባዊ ምኞቴ ነው” ብለዋል።

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሆነው በሀገሪቱ ከፍተኛ መማክርት (ካውንስል) በዛሬው ዕለት መሾማቸው ታውቋል፡፡

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን

ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሼክ ካሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያንን የሚተኩ ይሆናል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW