ጠ/ሚ ዐቢይ ለተደረገላቸው የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “በመላው ኦሮሚያ ስለተደረገው የአብሮነት ድጋፍ ድምጽ ከልብ አመሰግናለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የመንግስት ልዩ ተልዕኮ ህዝብን ማገልገል ብቻ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በየደረጃው ያለን የህዝብ አገልጋዮች ከእንደዚህ አይነት ድጋፍ የምንማረው እና መገንዘብ ያለብን ሀላፊነታችንን በአግባቡ እንድንወጣ የህዝብ ጥሪና አደራ እንዳለብን ሊሆን ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።