ጠ/ሚ ዐቢይ በአማራ ክልል የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት አደነቁ

ሚያዝያ 7/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአማራ ክልል የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት አደነቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት “በአማራ ክልል የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ከፍተኛ ጥረት አደንቃለሁ” ብለዋል፡፡
አክለውም በመላው ክልል ከ41ሺሕ ሄክታር በላይ ሲያለሙ በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ ከ2 ሺሕ 800 ሄክታር በላይ ምርታማነት መኖሩ አበረታች ነው በለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በክላስተር የግብርና አካሄዳችን በአንድነት ለምግብ ዋስትና እና ለሀገር ልማት ምን እንደምናሳካ ማሳያ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡