ጠ/ሚ ዐቢይ በፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ ከሚመራው ልዑክ ጋር ተወያዩ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐመድ ከሚመራው የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ልዑካን ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት እና ቁርጠኝነትን ገልጸዋል።

በተለይም የአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ እንዲሆን አብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ በትኩረት መወያየታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከአዲሱ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አስተዳደር ጋር በተለያዩ ደረጃዎች ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፤ በተለይም ለኢኮኖሚ ዕድገት አጽንዖት ሰጥተዋል።

ጠንካራ እና የተረጋጋች ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ጥንካሬ የሚጠቅም መሆኑንም ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን የጋራ ችግሮች ለመፍታት የትብብር አስፈላጊነትን አመልክተዋል።