ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ 100ኛ የምስረታ በዓል የእንኳ አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ 100ኛ የምስረታ በዓል

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለ100ኛው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ (CPC) የምስረታ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በራሳቸውና በፕሬዝዳንትነት በሚመሩት የብልጽግና ፓርቲ ስም አስተላልፈዋል።

ከ100 ዓመት በፊት የነበረው ራዕይ በቻይና ወንድ እና ሴት ልጆች ሀገሪቱን ለማበልጸግ የተጀመረው ስራ በጠንካራ እና ከልቡ በሚሰራ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራር አማካኝነት ዛሬ ትክክለኛው መስመር ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

በዚሁም በፓርቲው በብስለትና ጠንካራ አመራር ተንሰራፍቶ የነበረውን ድህነትን በመቀስ የቻይናውያን ህይወት በእጅጉ ማሻሻል መቻሉን አንስተዋል።

በዚህም የቻይና እድገትና ውጤታማነት በግላቸው መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የቻይና እድገት ለአፍሪካውያንም በጋራ ማደግ እሳቤን በመፍጠር ተጠቃሽ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጽ ለኮሙዩኒስት ፓርቲው የ1 መቶ አመት በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

በተመሳሳይ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ለቻይናው ኮሙዩኒስት ፓርቲ 1 መቶኛ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፓርቲው በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማድነቅም እንዲቀጥል እና በቀጣይ በጋራ እንደሚሰሩም አቶ ብናልፍ ገልጸዋል።