ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኡጋንዳ ገቡ

ነሐሴ 23/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በኡጋንዳ ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡