ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሓምዶክ እና ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን በትዊተር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል።

መሪዎቹ በ38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት በዛሬው እለት ጂቡቲ ገብተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል።

ጉባኤው በአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።