ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ነገን የመወሰን መብታቸውን እንድጠቀሙ አበረታቱ

ግንቦት 06/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ነገን የመወሰን መብታቸውን እንድጠቀሙ አበረታቱ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ5ኛው ብሔራዊ ምርጫ ተመዝጋቢዎች ቁጥር እየበለጠ እንደሚገኝ ገልጸው፣ የምርጫ ካርድ ለመውሰድ ያልተመዘገባችሁ ነገን የመወሰን መብታችሁን እንድትጠቀሙ አበረታታለሁ ብለዋል፡፡
ባለፉት ሳምንታት በ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡት ዜጎች መልካም ማድረጋቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳስበዋል፡፡