ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ሜጀር አውፖ ጄሲያ ሮዝ ኢፔልን ተቀብለው አነጋገሩ

የካቲት 13/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ሜጀር አውፖ ጄሲያ ሮዝ ኢፔልን ተቀብለው ማነጋገራቸውን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ በውይይታቸው ወቅት በቀጣናዊ እና በሁለትዮሽ የጋራ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ ተለዋውጠናል ብለዋል።