ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ፕሬዚደንት ሞሀመዱ ቡሀሪ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል አመሰገኑ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የናይጄሪያው ፕሬዚደንት ሞሀመዱ ቡሀሪ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል አመሰገኑ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሶ ሮክ በተሰኘው የፕሬዚደንት ቤተ መንግሥት በፕሬዚደንት ሞሀመዱ ቡሀሪ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “ወንድሜ ሞሀመዱ ቡሃሪ ስላደረጉልኝ ደማቅ አቀባበል አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው  “ሁለት ታላላቅ የአፍሪካ ሀገራት እንደ መሆናችን፣ የኛ ትብብር መጠናከሩ ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን እንዲሁም ለአህጉራዊ ትብብር ወሳኝ ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ልዑካን ቡድናቸው ከናይጄሪያው ልዑካን ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት  ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡