ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳኑ የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡሁራን ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡሁራን ጋር የተወያዩት በናይሮቢ እየተካሄደ ካለው 39ኛው የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።