ጠ/ሚ ዐቢይ ዜጎች ለአቅመ ደካማ ማህበረሰቦች እፎይታ ለመስጠት በሚደረጉ ጥረቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

ጠ/ሚ ዐቢይ

ነሀሴ 22/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁሉም ዜጎች ለአቅመ ደካማ ማህበረሰቦች እፎይታ ለመስጠት በሚደረጉ ጥረቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ከአምስት ሳምንታት በፊት ዓመታዊውን የቤት  እድሳት መርኃ ግብር በአዋሬ አካባቢ  መስጀመራቸውን አስታውሰው፣ ዛሬ ጠዋት እድሳታቸው  የተጠናቀቀ ቤቶችን ቀድሞ ባዘመመ ጎጆ  ይኖሩ ለነበሩት አረጋውያን አስረክበናል ብለዋል።