ጠ/ሚ ዐቢይ የአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ የጀመረችውን መጨረስ እንደምትችል ያሳየ ነው አሉ

ሰኔ 14/2014 (ዋልታ) የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ኢትዮጵያ የጀመረችውን መጨረስ እንደምትችል ያሳየ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አራተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ “አሻራችን ለልጆቻችን” በሚል መሪ ሀሳብ በሚተገበረው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ የተያያዘ ሲሆን እስካሁን ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴን ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ ለመርኃ ግብሩ መሳካት ቅድመ ዝግጅቶች በጊዜ መጠናቀቃቸው ተነግሯል።

በማስጀመሪያው መሠናዶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የቀድሞው ርዕሰ ብሔር፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳፋኪ መሐመትና የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

በአስታርቃቸው ወልዴ