ጠ/ሚ ዐቢይ የጓሮ አትክልት ሥፍራዎች እንዲኖሩ ማድረግ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር ወሳኝ ነው አሉ

መጋቢት 27/2014 (ዋልታ) የጓሮ አትክልት ሥፍራዎች እንዲኖሩ ማድረግ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የጓሯችን ስፋት ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን ወይም ጓሮ ባይኖረን እንኳ፣ ከተሞቻችን ዕድገታቸውን ሲቀጥሉ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የተመጣጠነ አመጋገብን እውን ለማድረግ በቤት ውስጥ የጓሮ አትክልት ሥፍራዎች እንዲኖሩ ማድረግ የከተማ ግብርናን ለማጠናከር ወሳኝ ነው።” ብለዋል
በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ በሚውሉ ቁሳቁስ አማካኝነት ወደላይ የሚዘረጉ የአትክልት ቦታዎችን መሥራት ለብዙኃኑ ቀላል ነው ሲሉም አክለዋል።
ቤተሰቦች ይህንን የማድረግ ዐቅማቸውን እንዲፈትሹና እንዲጠቀሙበት አበረታታለሁ ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡