ጨፌው የክልሉን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለማስተዳደር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ

መጋቢት 13/2014 (ዋልታ) ጨፌ ኦሮሚያ የክልሉን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለማስተዳደር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ።

ጨፌው 1ኛ ዓመት 6ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ሀብት አስተዳደር ኃላፊ መስታወት ፈይሳ ጨፌው በጉባኤው በክልሉ የሚገኙ የልማት ድርጅቶች በሚፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግ፣ ያለውን የገበያ ክፍተት ለመሙላት እና የልማት ድርጅቶችን ለማጠናከር አዋጁ መውጣቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የልማት ድርጅቶቹ ትርፋማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና በተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ታስቦ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

የቀረበው አዋጅ በ442 አብላጫ ድምፅ ሲፀድቅ በዛሬው ውሎ ጨፌው 3 አዋጆችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሚልኪያስ አዱኛ