ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያዩ

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

ታኅሣሥ 19/2015 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከቱርክ አቻቸው ያሳር ጉለር ጋር በሁለቱ አገራት ወታደራዊ ግንኙነቶች እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በቱርክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራ ልዑካን ቡድን የቱርክ መከላከያ ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውሮ የጎበኘ ሲሆን ኢንዱስትሪዎቹ ለመከላከያ ኃይሉ ዘመናዊነት እና ለቱርክ ዕድገት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ተመልክቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት የሚያጎለብት ከመሆኑም በላይ መልካም ወታደራዊ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ከመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡