ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አንድነትን የሚፈታተኑ ጉዳዮችን መታገል ይገባል አሉ

ሚያዝያ 21/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተኑ ጉዳዮችን መታገል እንደሚገባ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጫምባላላ በዓል አከባበር ላይ ተገኝተው ባረጉት ንግግር አሳሰቡ፡፡

የሲዳማ ሕዝብ ለረዥም ዓመታት ሲያቀርብ ለነበረው በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ሳይሰጠው ስለመቆየቱ አስታውሰዋል።

ለውጡን ተከትሎ ሲዳማ በክልል የመደራጀት ጥያቄው ተመልሶለታል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የክልሉ ነዋሪ ለሰላም እና ለልማት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ነው ያሉት።

የአገርን አንድነት የሚፈታተኑ ጉዳዮችን በጋራ መታገል እንደሚገባም አሳስበዋል።

በኃይሉ ጌታቸው (ከሀዋሳ)