ፋውንዴሽኑ በቦሌ ክፍለ ከተማ የጽዳት መርኃ ግብር አከናወነ

ግንቦት 27/2014 (ዋልታ) ኢልኔት ፋውንዴሽን የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀንን ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ የጽዳት መርኃ ግብር አከናወነ፡፡

የመርኃ ግብሩ ዋና ዓላማ አካባቢን ማጽዳት እና ስለ አካባቢ ጽዳት ግንዛቤ መፍጠር እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ድርጅቱ በዋናነት አቅመ ደካሞችን መርዳት፣ ለወጣቶች የሥራ እድልን መፍጠር፣ በተለይም ጎዳና ላይ የወደቁ ልጆችን ማገዝ እንዲሁም የአከባቢ ጥበቃ ላይ በትኩረት መስራት መሆኑን የፋውንዴሽኑ መስራች ጄሲካ ሄድማን ገልጸዋል።

ፋውንዴሽኑ የዓለም ቀንን ምክንያት በማድረግ ደረቅ ቆሻሻዎችን ከአከባቢ የማስወገድ ሥራ ማከናወኑ ነው የተገለፀው፡፡

በጽዳት መርኃ ግብሩም አከባቢን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ አዕምሮም ሊፀዳ እንደሚገባውም መልዕክት ተላልፏል፡፡

በእመቤት ንጉሴ