ፑቲን ለጆ ባይደን የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

አሸናፊው በውል እስኪለይ ዝምታን የመረጡት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ፑቲን እንኳን ደስ አለዎ መልእክት ያስተላለፉት የጆ ባይደንን አሸናፊነት ትናንት መታወጁን  ተከትሎ ነው፡፡

ባይደን ከ50 ግዛቶች 306 የወኪል ድምጽ ሲያገኙ ትራምፕ ግን 232 ላይ መቆማቸውን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡