ፓን አፍሪካ የተሰኘ የፎቶ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለዕይታ ክፍት ሆነ


ግንቦት 17/2014 (ዋልታ)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀው ፓን አፍሪካ የፎቶ አውደ ርዕይ ለዕይታ ክፍት ሆነ፡፡
በፎቶ አውደ ርዕዩ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የፓን አፍሪካ አቀንቃኞች ተገኝተዋል።
በኢትዮጵያ ጥናት ኢኒስቲትዩት ለአንድ ዓመት ያህል ሲዘጋጅበት የቆየው የፎቶ አውደ ርዕይ ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካ ያደረገችው አስተዋፅዖ ማሳየት የሚያስችሉ ሰነዶችና ፎቶ ግራፎችን ያካተተ ነው ተብሏል።
አውደ ርዕዩ ዛሬ እየተከበረ ያለውን የአፍሪካ ቀን አስመልክቶ የተዘጋጀ እንደሆነም ተመላክቷል።
በምንይሉ ደስይበለው