ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡ ሴት መሪዎችን አበረታቱ

የኢፌድሪ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የአመራር ስልጠና ማዕከል “አሙጃኤ” መርሀ ግብር ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡት ሴት መሪዎች አበረታተዋል።

ማዕከሉ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራትና ዘርፎች የተወጣጡ ሴት መሪዎችን በማሰልጠንና አቅማቸውን በመገንባት ብቁ ሴት መሪዎችን የማፍራትን አላማ የያዘ መሆኑ ተገልጿል::

ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ሴቶችን ለመደገፍና ለማብቃት ካስጀመሯቸው መርሀ ግብሮች የአመራር ስልጠና አንዱ እንደሆነ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውሷል::