ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ከፊፋ የተገኘ የእግር ኳስ ትጥቅ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ታዳጊዎች አበረከቱ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በፊፋ ስም ያገኙትን የእግር ኳስ ትጥቅ በአዲስ አበባ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ 600 ለሚጠጉ ታዳጊ ወጣቶች አበርክተዋል።

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ዋና ጸሐፊ ፋትማ ሳሙራ አማካኝነት የተገኘውን የእግር ኳስ ትጥቅ ከተረከቡ በኋላ ነው ፕሬዝዳንቷ ለታዳጊዎቹ ድጋፉን ያበረከቱት።

በርክክቡ ወቅት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ለታዳጊዎቹ ባደረጉት ንግግር ስፖርት በተለይም የእግር ኳስ ከተለያየ ቦታ መጥቶ ለሕግ ተገዢ ሆኖ ተደጋግፎ የጋራ ድል ማስመዝገብ፣ ከተሸነፉም ለሚቀጥለው ውድድር መዘጋጀትን ያስተምራል በማለት ሕይወታችሁን ለመምራት ተጠቀሙበት ብለዋል።

ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ትጥቁን ለእግር ኳስ ክለቦች ማስረከባቸውን ከጽህፈት ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።