ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፣ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የመንግሥታቱ ምክትል ዋና ፀሐፊ ሠመራ ገቡ

የካቲት 2/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆና የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ዛሬ ሠመራ ከተማ ገቡ።

ሠመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በቆይታቸው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።