ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ፀረ ሙስና ትግል የሥነ ምግባራዊ አሠራር ባህል ለመፍጠር ነው አሉ

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ

ታኅሣሥ 1/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፀረ ሙስና ትግል ሥነ ምግባራዊ አሠራር ባህል ለመፍጠር ነው አሉ፡፡

ፕሬዝዳንቷ በቲውተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሙስናና ብልሹ አሠራር ካለ ሠላም፣ መረጋጋት፣ ልማት እንዲሁም ጠንካራ የሥራ ባህል አይኖሩም፤ ሙስናን መዋጋት የዜጎች ሁሉ ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡

ዘንድሮ የሚከበረው ዓለምዐቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “በሥነ ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ነው::

አመራር ፀረ ሙስና እቅዶችን በመንደፍና በማስፈጸም ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡