ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማሪያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ውድድር የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ

የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት የፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማሪያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ውድድር የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ፡፡

ሲን፣ሰሰ በዝግጅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጺዮን ተክሉና ጥሪ የተደረገላቸው ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆነ የአፍሪካ አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባደረጉት ንግግር መንግስት ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማሪያምን ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነርነት ለመወዳደር ብቃትና ችሎታ ያላቸው ስለሆኑ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

እጩ ተወዳዳሪዋ ፕሮፌሰር ሂሩት በበኩላቸው ቢመረጡ ሊያሳኩ ያሰቡትን ራዕይ ዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የትምህርት ደረጃቸው፣ በመንግስትና በግል ያላቸው ከፍተኛ ሀላፊነት ደረጃና ሰፊ ልምድ ለውድድሩ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚመጥኑና አግባብነት ያላቸው እጩ ተወዳዳሪ መሆናቸውና በቀድሞ በስራ ባለደረቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መገለፁን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡