ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በ19ኛ ዙር ያሰለጠናቸን ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል

ሐምሌ 23/2014 (ዋልታ) ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 1ሺሕ 690 ተማሪዎች በዛሬው እለት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
ከ19ኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 997 ሴቶች ሲሆኑ 693 ወንድ መሆናቸው ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ላይ መሰረት ያደረገ ሥራን ሲሰራ መቆየቱን ያነሱት የዩኒቨርሲቲው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፈይሳ አራርሳ በዚህም ሀገርንና ወገንን መጥቀም የሚችሉ እና ዘመኑን የዋጀ እውቀትን ያካበቱ ትውልዶችን ማፍራት መቻሉን ገልፀዋል።
ተመራቂ ተማሪዎች የሀገርን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሀገርን እድገት አንድ እርምጃ ከፍ በሚያደርግ ተግባር ላይ መሰማራት ይገባቸዋል ብለዋል።
ከዚያ ባሻገርም ተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን ለመቀላቀል በሚደረገው ርብርብ መካከል ከሥራ ፈላጊነት አባዜ በመውጣት የሥራ ፈጣሪነትን ብሂል መተግበር ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
ሔብሮን ዋልታው (ከአዳማ)