ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ የበይነ መረብ ትምህርት መጀመር

ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ የበየነ መረብ የትምህርት መርኃግብር ጀመረ።

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የበየነ መረብ ትምህርት ለመስጠት ፍቃድ ያገኘ 5ኛ ዩንቨርሲቲ ነው።

የዩኒቨርሲቲ ዋና ስራ አስኪያጅ ፈይሳ አራርሳ አለም በዲጂታላይዜሽን መጥቃለች፤ ሀገራችን ያደጉ ሀገራት የደረሱበት እንድትደርስ ቴክኖሎጂን ማዘመን ይገባናል ብለዋል።

ዜጎች ጊዜያቸውን የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ብቻ በመጠቀም ባሉበት ሆነው ራሳቸውን እንዲያስተምሩና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

የትምህርት መርኃግብሩን ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲው ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ግብዓቶች ማሟላቱም ተነግሯል።

በመስከረም ቸርነት