ሀገር አቀፍ የአይ ሲ ቲ ልማት ፎረም በድሬዳዋ

ሀገር አቀፍ የአይ ሲ ቲ ልማት ፎረም በድሬዳዋ

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋቋሙለትን ዓላማ ለማሳካት የሚያግዝ ሀገር አቀፍ የቢዝነስና የአይ ሲ ቲ ልማት ፎረም ዛሬ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።

ፎረሙን ያዘጋጁት የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው።

የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ፎረሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቆሙላቸውን መሠረታዊ ዓላማዎች ትርጉም ባለው መንገድ ለመፈፀም ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልጸው፣ “አይ ሲ ቲ መጠቀም ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።

ፎረሙ በ2014 የትምህርት ዘመን አይ ሲ ቲን ለማስፋፋት የተያዙ ፕሮጀክቶችን ስኬታማ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑንን አስታውቀዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በፎረሙ ከ40 ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ከ350 በላይ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን፣ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ዳይሬክተሮችና የመስኩ ምሁራን፣ የተለያዩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።