“ሃይማኖት ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 15/2014 (ዋልታ) በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ሃይማኖት ለሰላም” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛሉ።

በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች እንዲሁም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የመጡ የሃይማኖት አባቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በመድረኩ በሃይማኖትና የሰላም ቁርኝት እንዲሁም በሰላም ግንባታ የእምነት ተቋማትን ሚና የሚያስቃኝ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎም ይጠበቃል።

በሳራ ስዩም