ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማጣራት ይኖርበታል-  ብልፅግና ፓርቲ

ብልፅግና ፓርቲ

ህብረተሰቡ ማንኛውንም ጉዳይ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎችን ትክክለኛነት በጥንቃቄ ማጣራት ይኖርበታል አለ ብልፅግና ፓርቲ፡፡

ፓርቲው ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በመላው አለምም ሆነ በአገራችን በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ሃሰተኛ ወሬዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ ብሏል፡፡

ማንኛም ዜጋ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎችን ከመቀበሉ በፊት ከተረጋገጠና ከትክክለኛ ምንጭ የተገኙ መሆናቸውን በጥንቃቄ ማጣራት አለበት ብሏል ፓርቲው፡፡

ከሰሞኑ የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር የሆኑትን የዶ/ር አብይ አህመድን ጤንነትና ደህንነት አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የተናፈሰው ወሬ ፍጹም መሰረተ ቢስና ሆን ተብሎ ህብረተሰቡን ለማደናገር ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የተሰራጨ ነውረኛ የሀሰት መረጃ ነው ሲል ገልጿል፡፡

ህዝቡ ለወደፊቱም ከተመሳሳይ ሀሰተኛ ወሬዎች መጠንቀቅ ይኖርበታል ሲል አሳስቧል፡፡

ህብረተሰቡን የማደናገርና ውዥንብር የመፍጠር ዓላማ ይዘው ሃሰተኛ ወሬዎችን እየፈበረኩ የሚያሰራጩ የጥፋት አካላትን በጥብቅ ተከታትሎ የህግ ተጠያቂ ማድረግ የመንግሥት ሃላፊነት ይሆናልም ብሏል፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን

https://www.facebook.com/waltainfo

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/WALTATVEth

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን

አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!