ህወሃት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እየደረሰበት ነው – አብን

ነሃሴ 5/2013 (ዋልታ) –የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት እየደረሰበት መሆኑን በጦር ግንባር ተሰልፈው እየተሳተፉ የሚገኙት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን ) የአደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊ ጋሻው መርሻ ገለጹ፡፡

አቶ ጋሻው ትናንት በነበረው ውጊያ ጠላት ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰበት ገልጸው ከመከላከያ ዘርፈዋቸው የነበሩ የጦር መሳሪዎች አመድ ሆነዋል ብለዋል፡፡

“አሁን ውጊያ እየተደረገ ያለባቸው አካባቢዎች ህወሃት እጅግ በጣም የተዳከመና የመከላከል ደረጃ ላይ መሆኑንና በአንጻሩም፤ የወገን ጦር በከፍተኛ መነቃቃት ላይ እንደሚገኝ ሊገነዘቡ ይገባል” ብለዋል፡፡

ህዝቡ አካባቢውን ባለመልቀቅ፣ የኢትዮጵያን ሰራዊት በመደገፍ፣ ለኢትዮጵያ ሃይል ትብብር በማድረግና መውጫ መግቢያቸውን በመጠቆም እገዛ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም አመልክተዋል፡፡

በትግሉ ህዝባዊ ሃይሉ ያለው መናበብ የሚያስደስት መሆኑን ገልጸው ምናልባት በቃላት ለመናገር አስቸጋሪ ነውብለዋል።

” በአካል የምታየውን ወኔና ጽናት በቃላት ለመግለጽ በጣም ይከብዳል” አቶ ጋሻው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡