ነሐሴ 20/2013 (ዋልታ) – የጌዴኦ ዞን ነዋሪዎች በዲላ ከተማ የህወሓትና ኦነግ ሸኔን የሽብር ቡዱኖች የሚያወግዝና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።
ነዋሪዎቹ ሀገሪን ከጥፋት ሀይሎች ለመታደግና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው ከመቀጠል በተጨማሪ እስከ ህይወት መስዋዕትነት ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የሽብር ቡድኖቹ በኢትዮጵያ የወጠኑትን እኩይ ተግባር በኢትዮጵያውያን በተባበር ክንድ ይፈርሳልም ሲሉ በመፈክር ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከፈተናዎቹ በላይ ሀያል ሀገር ናት ያሉት ነዋሪዎቹ በሽብር ቡዱኑ እንደማትፈርስ በመግለጽ ሀገር እያስከበረ ላለው ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን ከጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።