ህወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር ነዳጅ መዝረፉን የመንግሥታቱ ድርጅት ገለጸ

ስቴፋን ዱጃሪክ

ነሐሴ 18/2014 (ዋልታ) ህወሓት መቐለ ከሚገኘው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከር (570 ሺሕ ሊትር) ነዳጅ መዝረፉን የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ የአንቶኒዮ ጉተሬስ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ገለጹ፡፡

በቦታው የነበሩ የመንግስታቱ ድርጅት እርዳታ ሰጪዎች ዝርፊያውን ማስቆም እንዳልቻሉ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ክምችቱ ምግብ፣ መዳበሪያን እና አስፈላጊ የሰብአዊ እርዳታ ቁሳቁስን ለማጓጓዝ የሚውል መሆኑም ተገልጿል፡፡

የነዳጁ በህወሓት ቡድን መዘረፍ ለአከባቢው ማኅበረሰብ የሚሰጠውን ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚጎዳውም አመላክቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ለሰብዓዊ ሥራ ሊውል የነበረው ነዳጅ ላይ የተፈፀመውን ዝርፊያ አጥብቆ እንደሚያወግዝም ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW