ህወሓት በላይ ጋይንት ያወደመው የየኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት ነው

ነሀሴ 22/2013 (ዋልታ) – የህወሓት የሽብር ቡድን በላይ ጋይንት ያወደመው የየኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት እየተደረገለት መሆኑ ተገለጸ፡፡
ቡድኑ በነፋስ መውጫ የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጨምሮ በሌሎች የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ትራንስሚሽን መስመር ጥገና ክፍል ቡድን መሪ እንድርያስ ሽፈራው ገልጸዋል።
ከጥጥራ እስከ ነፋስ መውጫ ተዘርግቶ የነበረው ከ30 ኪሎ ሜትር በላይ የኤሌክትሪክ መስመር በጥፋት ቡድኑ መውደሙንም አቶ እንድርያስ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ከባድ የዝናብ ወቅት ቢሆንም የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባለሙያዎች መስመሩን ለመጠገን ሌት ከቀን እየሠሩ መሆኑን ነው የቡድን መሪው የተናገሩት።
የጉዳት መጠኑ ሠፊ በመሆኑ ከፍተኛ ወጪ እንደሚፈልግም ለአሚኮ ገልፀዋል።