ህወሓት ለዳግም ጦርነቱን የሚያስፈልገውን ሀብት ከየት አገኘ የሚል ጥያቄ ተነሳበት

ነሐሴ 19/2014 (ዋልታ) መሰረቷን በጀኔቫ ያደረገችው እና ለበርካታ መገናኛ ብዙኃን የምትሰራው ጋዜጠኛና ደራሲ አን ጋሪሰን ህወሓት በምስራቅ ግንባር የከፈተውን ጦርነት አስመልክታ ጥያቄ አንስታለች።

እንደ ጋዜጠኛዋ ህወሓት “ትግራይ ተከባለች፣ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይገባ ክልከላ ተደርጓል” የሚል ማደናገሪያ እያነሳ ባለበት ሰዓት፣ ጦርነቱን ዳግም ለመጀመር የሚያስችለውን ሀብት ከየት አገኘ ስትል በትዊተር ገጿ ባሰፈረችው ጽሁፍ ጠይቃለች።

ጦርነት ውድ እና ያልተቋረጠ መሳሪያ፣ ተተኳሽ፣ ተሽከርካሪ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የስለላ ቴክኖሎጂ እና ሌሎች አቅርቦቶች እንደሚፈልግ ጠቅሳ፤ በክልከላ ውስጥ ነኝ ሲል የሚከሰው ህወሃት ታዲያ እነዚህን አስፈላጊ ግብዓቶች ከየት አገኛቸው?” ስትል ጥርጣሬ አዘል ጥያቄዋን አጋርታለች።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ አን ትላንት የጦርነቱን መጀመር በሰማች ጊዜ ላነሳቸው ጥያቄ የተባበሩት መንግሥታት 570 ሺሕ ሊትር ነዳጅ የያዙ 12 ታንከሮቹ በህወሓት ተዘርፈውበት የሰብአዊ እርዳታ ስርጭቱን መስራት ከማይችልበት ደረጃ መድረሱን በመግለጽ በከፊል ምላሽ ሰጥቷታል፡፡

መሳሪያ እንደጫነ የተነገረለት የኢትዮጵያን የአየር ክልል አቋርጦ ሊገባ የነበረ አውሮፕላን መመታቱም ሌላኛው ፍንጭ ሰጪ መረጃ የሚሰጥ ምላሽ ነው መሆኑን ኢብኮ በዘገባው አመላክቷል።