ለህወሓት የሸብር ቡድን ለአፍታም ቢሆን የምንሰጠው ጊዜ አይኖርም – የምዕራብ ዕዝ

ነሃሴ 4/2013 (ዋልታ) – ለአሸባሪው የህወሓት ቡድን ለአፍታም ቢሆን የምንሰጠው ጊዜ አይኖርም ሲሉ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀነር ጀነራል መሠለ መሠረት ተናገሩ፡፡

ሜጀር ጀነራል መሠለ በዕዙ ውስጥ የሚገኘውን 314ኛ ኮር 31ኛ አድዋ ክፍለ ጦር እና 54ኛ ክፍለ ጦር የሠራዊት አባላት እየወሰዱ ያሉትን ስልጠና እና ወታደራዊ ዝግጁነት ተመልክተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም አሸባሪውን የህውሓት ቡድን ላለፉት 27 ዓመታት የተሸከምንበት ጀርባችን ተልጧል፤ ከአሁን በኃላ በህይወት እንዲኖር አንፈቅድለትም ብለዋል፡፡
አሸባሪውን የህውሓት ቡድንን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እየተቃወመው በመሆኑ ሠራዊቱ በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ስንቅ ይሆነዋልም ነው ያሉት፡፡
ህውሓት ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ እያለ የሚያሰራጨው ፕሮፖጋንዳ አሁን ያለበት ሁኔታ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ ቀርቶ እራሱን እንኳን ማደራጀት ያልቻለ ፍርክርክ ቡድን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሜጀር ጀነራል መሠለ ወታደሮች አሁን እየወሰዱት ያለው ስልጠና አሸባሪውን የህውሓት ቡድን በአጭር ጊዜ መደምሰስ የሚያስችል እና ጁንታው ዳግም በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ የሚያደርግ ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡