ለህግ ማስከበር ግዳጅ የተሠማራ ሚሊሻን ጨምሮ የ2 አቅመ ደካማ እናቶች ቤት የማደስ ተግባር ተከናወነ

አቅመ ደካማ እናቶች ቤት የማደስ ተግባር

ሐምሌ 18/2013 (ዋልታ) – ለህግ ማስከበር ግዳጅ የተሠማራ ሚሊሻን ጨምሮ የሁለት አቅመ ደካማ እናቶች ቤት የማደስ ተግባር ተከናወነ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሬዴሬሽን ምክር ቤት አመራርና ሠራተኞች በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ እፀገነት መንግስቱ ኢትዮጵያውያን የምንጋራቸው በርካታ እሴቶች ያሉ በመሆኑ አብሮነታችንን መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ምክትል አፈጉባኤዋ በባቢሌ ወረዳ የ3 አቅመ ደካሞ ቤተሰቦችን ቤት የመገንባት ስራም አስጀምረዋል፡፡

ለግንባታ ከተለዩ ቤቶች መካከል ደግሞ ለህግ ማስከበር ግዳጅ የተሠማራ ሚሊሻ ቤተሰብ ቤት ግንባታው አንዱ ነው፡፡

በባቢሌ ወረዳ በምክር ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች ከተከናወኑ የቤት ዕድሳት በተጨማሪ የከተማ ፅዳት በማከናወን በወረዳው ኤረር ጉዳ የቡና ምርጥ ዘር ማባዣ ከ2 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን ተክለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ በሚገኘው የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት  ተጠናክረው እንደቀጠለም ተገልጿል፡፡

(በሰለሞን በየነ)